የዋና ዳይሬክተሯ መልዕክት

 

IMG_8590.JPG

የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚንስትሮች ቤት ደንብ ደንብ ቁጥር 298/2006 የተቋቋመ ተጠሪነቱ ለትራንስፖርት ሚኒስቴር የሆነ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው.
በመዲናችን አዲስ አበባም ሆነ በተለያዩ የክልል ከተሞች የሀገራችንን የሀገራችንን ተከትሎ እየተበራከተ በመጣው የዜጎች የዜጎች ቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ ፍላጎት እንኳን ይገኛል .
ድርጅታችን አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ከመስከረም 5 ቀን 2007 ዓ.ም በፊት በተለይ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኛው በትራንስፖርት ዕጥረት ሳቢያ ይደርስበት የነበረው ችግር እጅግ በርካታ እንደነበር ለሁሉም ዜጋ ግልፅ ነው.
ፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኛው ምንም እንኳን በሰዓቱ ገብቶ መንግስትና ህዝብ የጣለበትን አደራ ለመወጣት ቢሞክርም በትራንስፖርት ችግር ሳቢያ ወደ ስራ ገበታው ይገባ የነበረው ከ 2: 30 ሰዓት በኋላ በመሆኑ በማርፈዱ የሚሰማው የህሊና ወቀሳ እንደተጠበቀ ሆኖ አገልግሎቱን ፈልገው ወደ ቢሮው የሚመጡ ባለጉዳዮችን ሰልፍ ሲመለከትና ችግሩ የመልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ መምጣቱን ሲገነዘብ ራሱን የችግሩ አካል በማድረግ በስራው ላይ እርካታ አልነበረውም
የዚህ ችግር መጠንና ስፋት እየጨመረ መምጣቱን የተረዳው መንግስት ምንም እንኳን ይህ መሰሉ አገልግሎት በሀገራችን አዲስ እንደመሆኑ መጠና ከሌሎች አለም ሀገራት ተሞክሮ ለማግኘት ባይቻልም ከችግራችን ተነስቶ ሀገራዊ መፍትሔ መሻት ግድ ስለሆነ ለፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኛው የትራንስፖርት አገልግሎት ለማቅረብ መንግስት ቃል ገባ . ቃሉም በአፋጣን ተግባራዊ ይሆን ዘንድ በተወሰነው መሠረት ድርጅታችን መስከረም 5 ቀን 2007 ዓ.ም በ 55 አውቶቡሶች አገልግሎት መስጠት ጀመረ.
የተጠቃሚው ቁጥር እየጨመረ የአገልግሎት ጥያቄውም እየተበራከተ መጥቶ ዛሬ ድርጅቱ ያሉት 410 አውቶቡሶች ሲሆኑ በሁሉም የመዲናችን አቅጣጫዎች በቀን በደርሶ መልስ ከ 82 ሺህ በላይ ሰራኞችን ጠዋት ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ ስራ ገበታቸው ማታም ከስራ ስፍራቸው ወደ መኖሪያ ቀያቸው ምቾታቸውን ጠብቆ በማጓጓዝ ላይ ይገኛል .
የምንሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎት በአገልጋይነት የተሞላ ግልፅና ግ ቀልጣፋ ይሆን ዘንድ ከባለድርሻ አካላትና ከህዝብ ክንፍ ልናርማቸው በሚገቡንን ግድፈቶች ዙሪያ ዘወትር እንነጋገራለን. በስልክና በግንባር በመቅረብም ዘወትር አስተያየቶቻቸውን ይገልፁልናልእኛም ልናስተካክላቸው የምንችላቸውን ሁሉ ባጭር ጊዜ ውስጥ አርመን መልሰን ወደ ተገልጋይ እናደርሳለን. አቅምንና ጊዜን የሚጠይቁ በቀጣይ የምንፈታቸውን የምንፈታቸውን ችግሮችን ደግሞ ወደ ፊት ምላሽ እንደሚያገኙ እጅግ ከምናከብራቸው ተገልጋዮቻችን ጋር በግልፅ በመወያየት አሰራራችን በአደባባይ እንዲሰጥበት ከተገልጋዮቻችን ጋር ከመቀራረብ አልፎ መስርተናል .
በመሆኑም ይህን ድህረ ገፃችን የምትጠቀሙ ተገልጋዮቻችንም ሆናችሁ ሌሎች አስተያየት ያላችሁ ዜጎቻችን ያለምንም ገደብ ያያችሁትን የተመለከታችሁትን እንዲህ ቢሆን ይህ ቢሻሻል የምትሉትን አስተያየትና ያለምንም ይሉኝታና ሀሳብ ትገልጹልን ዘንድ ግብዣዬ የአክብሮት ነው የምትሰጡንን ማንኛውም አስተያየቶች አቅም በፈቀደ መጠን ምላሽ እንደምንሰጥ በድርጅቱ ስም ቃል እየገባሁ ሀገራችን አሁን ለጀመረችው ልማትና ዕድገት የመነቃቃት ጉዞ ስኬት ትልቅ ዕምነትና ኃላፊነት የተጣለበት የፐብሊክ ሰርቫንቱን ሠራተኛ ከመቼውም ጊዜ በላቀ የአገልጋይነት ስሜት ለማገልገል መላው የድርጅታችን ሰራተኞች መነሳታቸውን እገልጻለሁ