አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች IFRS ለመተግበር ይረዳ ዘንድ የድርጅታችንን ቋሚ ንብረቶች የዋጋ ትመና ስራ በፕሮጀክቶች ደረጃ እንዲተገበር በተወሰነው መሰረት ቋሚ ንብረቶችን በአለም አቀፍ ዋጋ ትመና ስታንዳርድ /international valuation standard/ መሰረት በመገመት ከፍተኛ አስተዋፆ ላበረከቱ ሰራተኞች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጠ፡፡በመንገድ ላይ የትራፍክ አደጋን ለመከላከል የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሠራተኞችና የአዲስ አበባ ፖሊስ ትራፊክ ቁጥጥር አባላት የጋራ ምክክር አደረጉ፡፡ ‹‹መንግስት ሰራተኛውን አክብሯል፡፡››

ሀገራችን በእድገት ጎዳና ላይ ትገኛለች ፡፡ ከዘመናት በፊት ከሁሉ ቀድማ በአክሱም ላሊበላ፣ በጎንደር በየሃ የስልጣኔ ሻማ የለኮሰች ሀገር እጅግ በፈጠነ ሁኔታ ከድህነት ወለል በታች ወድቃ ተረጂና ተመፅዋች የነበረችበት ዘመን ያልፍ ዘንድ እጅግ በጀገነና በታተረ ትውልድ ታሪኳን ለመቀየር እየተከፈለ ባለ ሁለንተናዊ ትግል ዛሬ ሀገራችን በዕድገቷ እየተጠራች፣ ባላት የሰላም አየር እየተሞገሰች ትገኛለች፡፡ ይህ ለሀገራችን ለህዝቦቿ በአለም አቀፍ ደረጃ የተነገረ ክብሯ የሚገልፅ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...


“ህዝብን ከማገልገል የላቀ ምን አለ?”


ብዙዎቹ የባስ ካፒቴኖቻችን የረጅም ጊዜ ልምድና የማሽከርከር ዕውቀት ያላቸው ናቸው፡፡ መኪና ማሽከርከር መቻል ብቻ በቂ ዕውቀት እንዳልሆነ በተጨባጭ በሚታይበት በዚህ አደጋ በበዛበት ዘመን ለህግ ተገዥመሆንና ከዚያም በላይ በሃላፊነት ስሜት ማሽከርከር ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...


ቆይታ

ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ይታይ የነበረውን የትራፊክ ማኔጅመንት ሲቋቋም የማኔጅመንቱ ዋና የሥራ ሂደት ኃላፊ ሆነው ከአለም ባንክ በተገኘ ጥናት መነሻነት የፓርኪንግ አጠቃቀም የትራፊክ ፍሰትና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ከፖሊስና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ሰርተዋል፡፡ በፌደራል ትራንስፖርት ሚንስቴር የሚንስትሩ አማካሪ ሆነው ለረጅም አመት አገልግለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...