መምህር ነኝ፡፡ ከ3ዐ አመታት በላይ!! ከልጅነቴ ጀምሮ በምመኘው የቀለም አባትነት ሙያ ተሰማርቼ ሀገሬንና ህዝቤን በማገልገል ላይ አገኛለሁ፡፡ ወትሮም በልጅነቴ “ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ?” ሲባል ጓደኞቼ “ዶክተር ፣ ፓይለት ” ሲሉ እኔ “መምህር” ነበር የምለው፡፡ እናም ብዙዎቹ ይስቁብኝ ነበር፡፡ እኔ ግን እውነቴን ነበር፡፡ እናቴ “ምኞትህ እንኳን አያምርም” ብላ ብዙ ጊዜ ገርፋኛለች፡፡ እናቴ እውነቷን ነበር አባቴ አስተማሪ ሆኖ የረባ ኑሮ ሳይኖር እንደሞተ እያስታወሰች የምኞት ሃሣቤን ልታስቀይረኝ ብዙ ጊዜ መክራኛለች፡፡ ሲብሰባትም ገርፋኛለች እኔ ግን ……..