የፐቡሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ተልዕኮ ፣ ራዕይ እና እሴቶች

ዓላማ

1. በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ለአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት
2. ከስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ውጪና በእረፍትና በባዕላት ቀናት ለከተማው ህብረተሰብ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት
3. ከስራው ጋር ተያያዥና ተጓዳኝ የሆኑ ተግባራትን ማከናወን

 ራዕይ

በዘመናዊ የህዝብ የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ መርህ መሠረት ላይ ተዋቀረ ውጤታማ ድርጅት ለመፍጠር ለፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኛውና ለሌላው ህብረተሰብ በ2012 ዓ.ም ተደራሽ ፣ደህንነቱ ተጠበቀ ፣ምቹ፣ ቀልጣፋና ትርፋማ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ሆኖ ማየት ነው፡፡

ተልዕኮ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በፌደራልና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ መ/ቤቶች ለሚሰሩ ፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች በሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓቶች እንዲሁም ከስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ውጪና በእረፍትና በባዕላት ቀናት ለሌላው የህብረተሰብ ክፍል የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በተመጣጣኝ ታሪፍ የሚሰጥ ወጪውን በመቀነስና ገቢውን ለማሳደግ ከተቋቋመበት ዓላማ ግር ተዛማጅነት ያላቸውን አገልግሎቶች መስጠት ነው፡፡

ዕሴቶች

• የላቀ ጥራት ያለው አገልግሎት
• ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት በጋራ ስሜት ለውጤት
• በመልካም ሥነ-ምግባር ላይ የተመሰረተ ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት
• ፍትሐዊ ተደራሽነት እና ተጠያቂነት ያለው አገልግሎት
• ከአደጋ ተጠበቀ ደህንነቱና ምቾቱ የተረጋገጠ አገልግሎት