የድርጅቱ ታሪካዊ ዳራ 

የድርጅቱ ታሪካዊ ዳራ 

አጭር ቅኝት

በሀገራችን ተካሄደውን የስርዓት ለውጥ ተከትሎ እየተመዘገቡ ያሉ ሁለንተናዊ የዕድገት ውጤቶችና በሀገራችን እየተካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ ፈጣን እያደረጉት በመሄዳቸው በክልል ከተሞችና በተለይ ደግሞ አፍሪካና የሀገራችን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ከጭለት ወደ ዕለት እየተባባሰ የመጣው የትራንስፖርት ችግር አሳሳቢ እየሆነ መጣ፡፡

በተለይ በመዲናችን በተለያዩ የፌደራልና የአዲስ አበባ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች የችግሩ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ ከመሆናቸውም ባሻገር በዚሁ በትራንስፖርት እጥረት ሳቢያ መንግስት የመደበውን ስምንት ሰዓት የስራ ሰዓት ተግባራዊ ማድረግ ሳይችል በመቅረቱ አብዛኛው ሰራተኛ ወደ ስራ ገበታ የሚደርሰው ከ2፡30 ዘግይቶና በትራንስፖርት አጣለሁ ስጋት ከስራ መውጫ ሰዓት ቀደም ብሎ በመውጣቱ በሀገር ልማታዊ ዕድገት ላይ ከሚያስከትለው ጫና ባልተናነሰ አገልግሎት ፈልጎ ወደ መስሪያ ቤቶች የሚመጣው ዜጋ በመልካም አስተዳደር ችግር መጉላላቱን በጥናት ያረጋገጠው መንግስት ይህንን ችግር ለመቅረፍ ተግቶ እንደሚሰራ የሰርቪስ አገልግሎት ለፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኛው እንደሚያቀርብ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ለፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኛው በገቡት ቃል መሠረት ድርጅቱ በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 298/2006 ዓ.ም ተጠሪነቱ ለትራንስፖርት ሚንስትር ሆኖ ተቋቋመ፡፡ ድርጅቱ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 298/2006 ዓ.ም ከተቋቋመ በኋላ በቀጣይ የድርጅቱን አደረጃጀት እና መዋቅር የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ አደረጃጀት እና መዋቅሩ ከፀደቀ በኋላ ድርጅቱን የሚመሩ አመራሮች የመቅጠር እና የሥራ አመራር ቦርድ የመሰየም ሥራ ሥራዎች በቅደም ተከተል መከናወን ጀመረ፡፡ በተለይ ከሐምሌ 2006 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 5 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ በነበረው ጊዜ በጣት በሚቆጠሩ አመራሮች መንግስት ለፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኛው በገባው ቃል መሠረት የትራንስፖርት አገልግሎቱን በመስከረም ወር መጀመሪያ ለመጀመር ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በተገኘ አንድ ቢሮ ውስጥ በትውስት በተገኙ ውስን ጠረጴዛ እና ወንበሮች ባስ ካፒቴኖች ፣ የቴክኒክ ባለሙያዎች እና የኦኘሬሽን ባለሙያዎች በቅድሚያ ለመቅጠር በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ኮሪደር እና በረንዳ ላይ አመራሩ እና ጥቂት ሠራተኞች የተቀጣሪ ሠራተኞች ምዝገባ ፣ ኢንተርቪው እና ምልመላ አካሄዱ፡፡ የባለድርሻ አካላትንም በመሰብሰብ ድርጅቱ የተቋቋመበት ዓላማ እና ተልዕኮ በማስረዳት የፐብሊክ ሰርቪሱ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ በየተቋማቸው የሚገኘውን ሠራተኛ ዝርዝር የመኖሪያ አካባቢ ታክሲ ወይም አውቶቡስ የሚይዝበት ፌርማታ መስሪያ ቤታቸው የሚገኘበት ቦታ ልዩ ስም የያዘ መረጃ በሃርድ ኮፒ እና በሶፍት ኮፒ እንዲያቀርቡ ተደረገ፡፡ የኦኘሬሽን አመራሮች ይህን መረጃ በማጠናቀር ከመረጃው በመነሳት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥባቸው መስመሮች ለመዘርጋት 27 መነሻ እና 11 መድረሻ ቦታዎች እና የከተማው ዋና ዋና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ መንገዶች ተከትለው መስመር እንዲዘረጉ የውሣኔ ሃሣብ ቀረበ፡፡ የሥራ አመራር ቦርድ አባላትና ባለሙያዎች ከፍተኛ ተሳትፎና ድጋፍ ታክሎበት ቅዳሜ ፣ እሁድ ፣ ጨምሮ በበዓላት ቀናት ሳይቀር ሥራዎችን ወደ ቤት ይዞ በመሄድ ጥናቱን ወደ ተግባር ለመለወጥ በቁርጠኝነቱ ርብርብ በማድረጋቸው መስከረም 5 ቀን 2007 ዓ.ም አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊት አገልግሎቱን በተጠቀሰው ቀን ለመጀመር ለተጠቃሚዎች የትራንስፖርት መጠቀምያ ወረቀት የማዘጋጀት እና የማደል ሥራ ፣ የባስ ካፒቴኖች ስልጠና ፣ የአውቶቡሶች ርክክብ ፣ በመስመር መዘርጋት፡፡ ለአገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎች መስመር ባስ ካፒቴኖችን በመመደብ /እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሣኔ መሠረት ፈርሶ ሠራተኛው ወደ ፐብሊክ ስርቪስ እንዲመደብ የተደረገው የዋልያ ሠራተኛ ምደባ ሥራ/ በማካሄድ መስከረም 5 ቀን 2007 ዓ.ም አገልግሎት ለመጀመር ጠቅላላ አመራሩ አራቱንም ቅርንጫፎች ላይ በመከፋፈል የተሰራው የተቀናጀ ነበር፡፡ 55ቱ አውቶቡሶች በ10 መስመሮች ተሰማርተው በየምድብ መስመሮቻቸው ሲደርሱ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኛው እርካታና ደስታ በገፅታቸው ላይ ይነበብ ነበር፡፡ የሚዲያ ሰዎች ክንውኑን ሊዘግቡ የነበረው ትውሰታ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አመራር እና ሠራተኛው አሁንም ሥራችን በቁርጠኝነት እና በትጋት እንድንቀጥል ያነሳሳ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

ካጋጠሙን ችግሮች ዋና ዋናዎቹ

ባሳለፍነው አንድ ዓመት ካጋጠሙን ችግሮች ዋና ዋናዎቹ ለአገልግሎት መስጫ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለዴፖ የሚሆን ቦታ በፍጥነት አለማግኘት አንዱ ሲሆን ችግሩን በጊዜያዊነት ለመፍታትና ለአውቶቡሶች መዋያና ማሳደሪያ ቦታ ለማግኘት በየአካባቢው የሚገኙ ሰፊ ግቢ ካላቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ግንኙነት በመፍጠር ፣ በማስፈቀድ አመራሩ ባደረገው ጥረት ችግሩን በጊዜያዊነት በመፍታት አገልግሎቱ ለመጀመር ተችሏል፡፡ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ተጠቃሚ ተቋማት የሠራተኞቻቸው መረጃ በወቅቱና በሚፈለገው ጥራት አለማቅረብ በዚህ ምክንያት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ለተጠቃሚዎች አሟልቶ የትራንስፖርት መጠቀሚያ ወረቀት ለመስጠት አስቻጋሪ ስላደረገው ችግሩን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር እና መረጃዎች አሟልተው እንዲያመጡ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ለመጠበቅ ተችሏል ፡፡

ለፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኛው የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ያሰገኘው ውጤት

ለፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኛው የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ያሰገኘው ውጤት በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

  1. ለሠራተኛው ያሰገኘው ጥቅም ይደርስበት ከነበረው እንግልት ከፍተኛ የትራንስፖርት ወጪ እና በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት ስዓቱን አክብሮ ወደ ሥራ ባለመግባቱ ምክንያት ሲደርስበት የነበረው ስለልቦናዊ ጫና ማስቀረቱ ፤ ደህንነቱ ተጠብቆ ያለምንም ክፍያ በስዓቱ በሥራ ቦታው በመግባት ሕዝብ ማገልገል መቻሉ፤
  2. የመንግስት አገልግሎት ለማግኘት ወደ የመስሪያ ቤቱ ከሚሄደው ሕዝብ አንፃር የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አገልግሎት ከመጀመሩ በፊት በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት በስዓቱ ሠራተኛው ወደ ሥራ ባለመግባቱ ወይም ቀድሞ ከሥራ በመውጣቱ ተገቢው አገልግሎት ያለማግኘት መንገላታት እና መመላለስ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ሠራተኛው በስዓቱ ወደ ሥራ ስለሚገባ እና ስዓቱን አክብሮ ስለሚወጣ የሕዝቡ ችግር ተቀርፏል ማለት ይቻላል፡፡

የተቀመጠው ሁለተኛው የድርጅቱ ግብ

ድርጅታችን በተቋቋመበት ደንብ የተቀመጠው ሁለተኛው የድርጅቱ ግብ አውቶቡሶቻችን በሥራ መግቢያ እና መውጫ ስዓት ለፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኛው የትራንስፖርት አገልግሎት ከሰጡ በኋላ ባለው ሰዓት ለአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ሲሆን በዚህ መሰረት ጧት ቀን እና ማታ ተሣፋሪ በሚበዛባቸውና እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች አውቶቡሶች በማሰማራት በቀን ከ16 ሺ በላይ ሰዎች እያጓጓዝን ሲሆን ወደፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን፤ በከተማ ያለው የትራንስፖርት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የትራንስፖርት ስርዓቱ ወደ ቡዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ማደግ እና የተቀናጀ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ያሰፈልጋል፡፡