የዜጐች ቻርተር

መንግስት ዜጎችን የልማት እና የዕድገት ተጠቃሚ ለማድረግ እየወሰዳቸው ካሉት እርምጃዎች አንዱ ለፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች በሥራ መግቢያ እና መውጫ ስዓት ከቤት ወደ ሥራ እና ከሥራ ወደ ቤት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ሲሆን ይህንንም አገልግሎት ለመስጠት ተልዕኮ ተሰጥቶት የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅትን የልማት ድርጅቶችን ለማቋቋም ባወጣው አዋጅ ቁጥር 25/1984 በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 298/2006 አቋቁሟል፡፡ ድርጅታችን የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጀት የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኛው በከተማው ባለው የትራንስፖርት አገልግሎት እጥረት ምክንያት ይደርሰበት የነበረው ወከባ፣ እንግልት እና ወጪ በማሰቀረት ምቾቱና ደህንነቱ ተጠብቆ በሚፈለገው ጊዜ እና ፍጥነት በአስተማማኝ ሁኔታ ወደሥራው እና ወደቤቱ ለማድረስ እንዲችል የተለያዩ አሰራሮችን እና አደረጃጀቶችን በመዘርጋት ላይ ይገኛል፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ሠራተኞች እና ሌሎች ደንበኞች በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ለሚያቀርቧቸው ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋትና ተጠቃሚ መስሪያ ቤቶች እና ሠራተኞች በአገልግሎት አሰጣጡ ወቅት የሚኖራቸውን ተሳትፎ ለማሳወቅ መረጃዎች በአግባቡ እንዲደርሷዋቸው ለማድረግ የምንሰጠው አገልግሎት ግልጸነትና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ እንዲፈጸምና ድርጅታችን የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት የዜጎች የስምምነት ሰነድ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡
ስለሆነም የድርጀቱን የተጠቃሚ መስሪያ ቤቶች ፣ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሠራተኞች እና የሌሎች ደንበኞችን መብትና ግዴታ በግልጽ የሚያመለክት የዜጎች የስምምነት ሰነድ ወይም ቻርተር በሚከተለው አኳያ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

ሙሉውን የዜጎች ቻርተር ለማግኘት ይህን ዳውንሎድ ያድርጉ    የዜጐች ቻርተር ሕዳር 2 2008 ዓ.ም (pdf)