ተገልጋይ ምን ይላል?

ወደ ተለያዩ የፐብሊክ ሰርቪስ መስሪያ ቤቶችና ተቋማት ተንቀሳቅሰን የአንድ አመት ህዝባዊ አገልግሎታችን ምን ይመስል እንደነበር ለመጠየቅ ሞክረናል፡፡ ብዙዎች ቀደም ሲል ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት መውደቅና መነሳት ወደ ኋላ እያሰቡ መንግስት ይሄንን መልካም ተግባር ለሰራተኛው አስቦ አገልግሎት መጀመሩ በስራ ህይወታቸውና በማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ያመጣውን ለውጥ በተጨባጭ ምሣሌ እየጠቀሱ በምስጋና አውግተውናል፡፡ 

comments

 

ተገልጋይ ምን ይላል?

ወደ ተለያዩ የፐብሊክ ሰርቪስ መስሪያ ቤቶችና ተቋማት ተንቀሳቅሰን የአንድ አመት ህዝባዊ አገልግሎታችን ምን ይመስል እንደነበር ለመጠየቅ ሞክረናል፡፡ ብዙዎች ቀደም ሲል ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት መውደቅና መነሳት ወደ ኋላ እያሰቡ መንግስት ይሄንን መልካም ተግባር ለሰራተኛው አስቦ አገልግሎት መጀመሩ በስራ ህይወታቸውና በማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ያመጣውን ለውጥ በተጨባጭ ምሣሌ እየጠቀሱ በምስጋና አውግተውናል፡፡ 

comments

 

ታምራት ስዩም፤የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሰው ሀብት ጊዜያዊ ቡድን መሪ

 

ቀደም ሲል የፐብሊክ ትራንስፖርት ባልነበረበት ወቅት በታክሲ ስንጠቀም በጣም ተቸግረን ነበር፣ በሰዓቱ መግባትም ሆነ መውጣት አልቻልንም ነበር፡፡ በዚሁ ምክንያት ስራዎች ይበደሉ ነበር አሁን ግን አገልግሎቱ በመሰጠቱ በተገቢው ሁኔታ ሥራችንን እያከናወንን እንገኛለን፡፡ጅምሩ ጥሩ ነው ነገር ግን እኛ ዘንድ ያሉ የጤና ባለሞያዎች አብዛኞቹ ተጠቃሚ አይደሉም ምክኒያቱም ስራቸውን የሚያከናውኑት በሽፍት ስለሆነ የጥዋትና የማታው ዕድል አይደርሳቸውም ከተቻለ በሽፍት መግቢያና የመውጪያቸውን ሰዓት ታይቶ በተለየ ሁኔታ ቢመደብላቸው ጥሩ ነው፡፡

ወ/ሪት ማሜ ካሣ፤በአ/አ/ዩ/ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኤክስፐርት

ከአካል ጉዳትና ከሴትነት አንጻር በትራንስፖርት አጠቃቀም ላይ ብዙ ችግሮች አሉ፡- በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ስንጠቀም የመገፋት የመስረቅ ከዚያም ባለፈ በተለይ በአውቶቡሶች ውስጥ የፆታ ትንኩሳ ይፈፀምብናል በትራንስፖርት አጠቃቀም ላይ በሴቶች በተለይ በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚደርሰው እንግልት ከፍተኛ ነው፡፡አሁንም ይህ የትራንስፖርት ሂደት መጀመሩ ችግሩን አቃሎልናል ነገር ግን በፐብሊክ ሰርቪስ ውስጥ የምንጠቀመው የተለያዩ መስሪያ ቤት የምንሰራ ሰራተኞች ስንሆን በተለይ የመውጪያ ሰዓታችን የተለየ ሲሆን በጋራ ለመጓዝ ግን ቀድሞ የወጣው የሚዘገየውን ለረጅም ሰዓታት ይጠብቃል ይህ ጥናት ተደርጎበትና የተሸከርካዎቹ ቁጥር ተጨምሮ ችግሩ ቢቃለል ጥሩ ነው፡፡የፐብሊክ ሰርቪሱ ንጽህና ጥሩ ነው ካፒቴኑም ሆኑ ሌሎች ሰራተኞች የሚያደርጉልን እንክብካቤና አቀባበል በጣም ጥሩ ነው፡፡ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡

አቶ ተስፋዬ ሰለሞን፤ በአ/አ/ዩ/ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የወጪ ግንኙነት እቅድ ዝግጅት ኤክስፐርት

የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ 2500 ሰራተኞች የፐብሊክ ሰርቪስ ተጠቃሚዎች ናቸው ቀደም ሲል የትራንስፖርት ችግሩ በጣም ከፍተኛ ነበር፣ በሰዓት ገብቶ ስራዎችን መስራት አይቻልም ነበር ስራ ይበደላል ማታ ሲወጣ ደግሞ እቤታችን የምንደርሰው አምሽተን ስለነበር ለሌባና ቀማኛ እንዳረግ ነበር አሁን ግን ይህ ሁሉ ተቃሎ ሠራተኛው ያለስጋት ስራውን እየሰራ ነው፡፡የመንግስት ሰራተኛው አገልግሎት ከሰጠ በኃላ በክፍያ የሚጠቀሙት ተጠቃሚዎች ለሰርቪሱ ንፅህና የሚጨነቁ አይመስልም የተለያዩ ቆሻሻዎችን ውስጡ ይጥላሉ ስለዚህ በተቻለ አቅም እንደመንግስት ሰራተኛው ሁሉ በገንዘባቸው የሚጠቀሙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሰርቪሱን ንፅህና ቢጠብቁ ጥሩ ነው፡፡ ቁጥጥር የሚያደርግ አባል ቢኖር ችግሩ ሊቃለል ይችላል፡፡ ሌላው አንዳንድ ካፒቴኖች ሰራተኛው የሚጫንበትን እና የሚወርድበትን ፌርማታ የመዝለል፣ ከቦታው አርቆ የማውረድ ሁኔታ ይታይባቸዋል ሌላው ተጠቃሚው ጥዋትም ሆነ ማታ በተመደበው ሰዓትና ቦታ የመገኘት ግዴታ አለበት ይህ እንደችግር የሚታይ ስለሆነ ሊታረም ይገባዋል፡፡

ቅድስት ሀይሌ ፤ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ባህልና ቱሪዝም የሥራ ሂደት አስተባባሪ

ቀደም ሲል ሰርቪስ ባለመኖሩ በሰዓታችን ስራ አንገባም ነበር በዚህም ምክኒያት ከአለቆቻችን ጋር እንጋጭ ነበር፡፡የተመደቡት ፐብሊክ ሰርቪሶች ቁጥራቸው አነስተኛና ከመንግስት ሰራተኞች ቁጥር ጋር ተመጣጣኝ ባመሆናቸው ተሳፋዎቹ ተጨናንቀው ነው የሚጓዙት አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ በጭራሽ ያልተመደበባቸው ቦታዎች አሉ ስለዚህ ሁሉንም በእኩል ደረጃ ማስተናድ ይቻል ዘንድ ተጨማሪ አውቶቡሶችን ጥናት ተደርጎ ቢጨመር ጥሩ ነው፡፡

አቶ አፈወርቅ ቦጋለ ከልደታ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ፅህፈት ቤት

የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወዲህ በሰዓት ገብተን ስራችንን እንሰራለን እንደቀድሞው መሳቀቅ አለቃ አየኝ አላየኝ ማለት የለም ሂደቱ ጥሩ ነው፡፡

የተጠቃሚው ብዛትና የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶቡሶች ቁጥር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ተሳፋሪዎች ተጨናንቀው ነው የሚሄዱት ሌላው ደግሞ ጠዋት ወደመነሻ ለመድረስም ሆነ ማታ ከመድረሻው ወደቤታችን ለመግባት አካባቢያችን ራቅ ያለ ሰዎች በታክሲ የምንጠቀም ጊዜ አለ፡፡ ምክንያቱም አገልግሎቱ እስከ መጨረሻው ባለመሆኑ ስለዚህ የአውቶቡስ ቁጥር ከፍ ቢልና እስከ መጨረሻው ድረስ የሚሄድበት ሁኔታ ቢፈጠር ጥሩ ነው፡፡

ጥሩዓለም መኮንን፤ ከልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጽ/ቤት

ቀደም ሲል የትራንስፖርት ችግር በመኖሩ በሰዓቱ ቢሮ መግባት አንችልም ነበር፡፡ አሁን ግን በሰዓቱ እገባለሁ፡፡

እንደችግር የሚታየው የሰርቪሱ ቁጥር አነስተኛ መሆን ነው በመሆኑም ተጠቃሚዎች ተጨናንቀን ነው የምንጓዘው በቂ አይደለም፣ ሌላው ደግሞ ቅርብ ያሉና ሩቅ ያሉት እኩል ስለሚነሱ የሥራ መግቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት ቢሮ ይደርሳሉ ለረጅም ጊዜም ይቆያሉ ስለዚህ ቢቻል የመነሻ ሰአቱ እንደቦታው ርቀት ቢሻሻል፡፡

አቶ ግዛው ዓለሙ፡ በፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎትየሰሜን አገልግሎት መስጫ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ

የድርጅታችን ትልቁ ዓላማ ያለአደጋ በማሽከርከር ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት ነው፡፡ ከባስ ካፒቴኖቻችን ጋር በየሳምንቱ ተገናኝተን በመወያየት ያለአደጋ አገልግሎት የምንሰጥበት ሁኔታ እናመቻቻለን፡፡ በሚደርሱ አደጋዎች ዙሪያ ሪፖርቶችን መነሻ በማድረግ እንወያያለን ፣ አደጋ አድራሹ የባስ ካፒቴን ማብራሪያ እንዲሰጥበት እናደርጋለን፣ አደጋ ካልደረሰም ለካፒቴኖቻችን ስለመልካም የስራ አፈፃፀማቸው ምስጋና እናቀርባለን በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎችም ቀርበው ያመሰግናሉ፡፡ስለደንበኞቻችን አያያዝ፣ ስለአውቶቡስና የግል ንፅህና፣ ለካፒቴኖቻችን ስልጠና እንሰጣለን በዚህም ለውጥ ተገኝቷል፡፡

የኛ በሰሜን ቅርንጫፍ ስራችንን የጀመርነው በ17 አውቶቡስ ሲሆን በአንድ ወር ውስጥ 19 አደጋዎች ደርሰው ነበር አሁን ደግሞ በ46 አውቶቡስ ለመንግስት ሰራተኛውም ሆነ ለታክሲ ተጠቃሚው አገልግሎት እየሰጠን ምንም ዓይነት አደጋ የማይደርስበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ ይህም የሆነው በየወቅቱ ስልጠና ስለምንሰጥና ካፒቴኖቻችን የባህሪይ ለውጥ ስላመጡ ነው፡፡በቅርንጫፋችን 26 የ1ለ5 አደረጃጀት ሲኖር፣ በባስ ካፒቴኖችና በትኬት ቆራጮች በኩል ደግሞ 22 የ1ለ5 አደረጃጀት አለ፡- ሁሉም እቅዱን አዘጋጅቶ በየወቅቱ በስራዎቹ ዙሪያ ይወያያል፡፡ ችግሮቹን ይፈታል፡፡ ከአቅም በላይ ችግር ካጋጠመ ሪፖርት ያቀርባሉ በመሆኑም አደረጃጀቱ ውጤታማ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ባዘጋጀነው ፎርም መሰረት ከተጠቃሚው ስለአገልግሎታችን አስተያየቶችን እንሰበስባለን ደካማ ጎኖችን እናርማለን ጠንካራ ጎኖችን እንቀጥልበታለን፡፡

ስራችን በቀጥታ ከህብረተሰቡ ጋር የሚያገናኘን በመሆኑ የሰርቪሱ ተጠቃሚዎች ካቋቋሙዋቸው ኮሚቴዎች ጋር በየወቅቱ እየተገናኘን እንወያያለን፣ የሚያቀርቡትን ችግሮች አይተን እንፈታለን ይህ ደግሞ ለስራችን መቃናት ያደረገው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው፡፡የክፍለ ከተማ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ፣ የክፍለ ከተማ ፖሊስ፣ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ ትራፊክ ፖሊስ፣ ተራ አስከባሪዎችን ያካተተ ኮማንድ ፖስት አለን፡፡ በቀጠናችን በትራንስፖርት ዙሪያ በሚነሱ ችግሮች ላይ በጋራ ተወያይተው የመፍትሔ አቅጣጫ እናስቀምጣለን፡፡ ከተጠቃሚ መ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በመወያየት ችግሮችን እንፈታለን፡፡በቀጣይ ያለውን የአውቶቡስ እጥረትና የተጠቃሚውን ፍላጎት ለማጣጣም ተጨማሪ መኪኖች የሚኖሩበትን ሁኔታ እናመቻቻለን፡፡ ሌላው የ1ለ5 አደረጃጀትን አጠናክረን እንቀጥላለን እንዲሁም ከመ/ቤታችንና ከተጠቃሚው ምን እንደሚፈለግ መመሪያ አለን ይህን ሁሉም እንዲያውቀው ጠንክረን እንሰራለን፡፡

አቶ አለምሸት መሸሻ፤ በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ረዳት ኃላፊ

በዋና መ/ቤትና ቅርንጫፍ ቢሮዎች የሚገኙ 570 የሚደርሱ ሰራተኞቻችን ቀደም ሲል የሰርቪስ አገልግሎቱ ባለመኖሩ በጊዜ ቢሮ አይገቡም ነበር፡፡ ይህ ደግሞ አገልግሎት ፈላጊው ነዋሪ በተገቢው ሁኔታ አገልግሎት እንዳያገኝ አድርጎታል፡፡ አሁን ግን የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት በመኖሩ ሰራተኞቻችን በጊዜ ገብተው የተቀላጠፈ አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡ በዚህ መነሻነት መ/ቤታችን በ2007ዓ.ም በመልካም አስተዳደር ለውጥ ስራዎች ሞዴል ሆኖ ተመርጧል፡፡

ሠራተኞች በሰዓት ገብተው አገልግሎት እንዲሰጡ ከማስቻል ባለፈ ለትራንስፖርት የሚወጣውን ወጪ የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት አስቀርቷል ስለዚህ ይህ ሁኔታ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ሰራተኛው ደስተኛ ነው፡፡

ከፐብሊክ ሰርቪስ መ/ቤቱ የተላከልንን መመሪያ ማስታወቂያ ቦርድ ላይ በመለጠፍ ሰራተኞቻችን ግንዛቤያቸውን ከፍ ለማድረግ ሞክረናል፡፡

ይህ የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት ለብዙ ሠራተኞች እርስ በርስ እንዲተዋወቁ ፣ እንዲወያዩ ፣ የልምድ ልውውጥን እንዲያደርጉ ረድቷል፡፡ መረጃ እንድንለዋወጥ አግዞናል፣ ለአንድ ሀገር ዕድገት በጋራ እንድንሰራ አድርጎናል፡፡ ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡

ዘርትሁን በላይ፤ ሲኒየር የሰው ሀይል አስተዳደር ኦፊሰር

የትራንስፖርት ችግሩ ስራችንን በአግባቡ እንዳንሰራ፣ ገንዘባችንን ያለአግባብ እንድናወጣ፣ እንግልትና፣ ወከባ እንዲደርስብን አድርጎናል በተለይ በእኛ በሴቶች ላይ ይደርስ የነበረው ችግር ደግሞ ከፍተኛ ነበር፡፡ አሁን ግን መንግስት ባደረገልን ድጋፍ ያለ ክፍያ ጥዋት ወደ ቢሮ ማታ ወደ ቤታችን እንሄዳለን፡፡ ለትራንስፖርት እናወጣው የነበረውን ወጪም ለቤታችን የተለያዩ ጉዳዩች መጠቀም ጀምረናል፡፡ ሂደቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡

 

comments